አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

 ከመሬት በላይ 107 ሜትር ከፍታ ባለው የሕንፃ አናት ላይ እንገኛለን፡፡ ከሕንፃው አናት ላይ በመሆን አዲስ አበባን በሁሉም አቅጣጫ መቃኘት ይቻላል፡፡ ከአዲስ አበባ ብሔራዊ ስቴዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው አዲሱ ሕንፃ በከተማው ከበቀሉ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች አንዱ ሲሆን፣ ሕንፃውን ያስገነባው የወጋገን ባንክ ኃላፊዎችም የከተማውን ረጅም ሕንፃ ዕውን እንዳደረጉ ይናገራሉ፡፡

የአገሪቱ የወተት ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለያዩ ችግሮች እንደሚታዩ ሲገለጽ ሰነባብቷል፡፡ በወተት አቅራቢዎችና በወተት አቀነባባሪዎች መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ጤና ማጣቱ በወተት አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚና በአዲስ መዋቅር ሁለት ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎች ተሰየሙለት፡፡ በቅርቡ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው የተገለጸውን የምርት ገበያውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጨምሮ፣ ሌሎች ሁለት የምርት ገበያው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በላቸው መኩሪያ (ዶ/ር) በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የተመለከተ ወቅታዊ መግለጫ ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ሰጥተው ነበር፡፡

በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ትልልቅ የሚባሉ የግንባታ ሥራዎችን በማከናወን የሚታወቀው በቻይና መንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደረው ቻይና ኮንስትራክሽን ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን (ሲሲሲሲ)፣ በግሉ እየገነባ ያለውን የኢንዱስትሪ ፓርክ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአገሪቱ ትልቁ የሚባለውን የአዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚያካሂዳቸውን አራት የንግድ ትርዒቶች ከቀደመው ጊዜ በበለጠ ለማሰናዳት መዘጋጀቱን ገለጸ፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ ይኼን ያስታወቀው ባለፈው ሐሙስ የሦስቱን የንግድ ትርዒቶች መርሐ ግብር ይፋ ባደረገበት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባዘጋጀው በዘንድሮው የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት፣ የውጭ ኩባንያዎች ተሳትፎ እንደሚጨምርና ከአሥር አገሮች የሚመጡ ኩባንያዎችም በዓውደ ርዕዩ እንደታደሙ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ከተሰማ በኋላ የምርት ገበያው የቦርድ አመራሮች ከሠራተኛው ጋር ባደረጉት ውይይት ቀጣዩን የምርት ገበያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በቅርቡ እንደሚሰየሙ ማስታወቃቸው ተገለጸ፡፡

Pages