አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ችግሮቹ?

በገነት ዓለሙ

“ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ” የተሰኘችው ኢትዮጵያ ነፃ የሆኑ የተለያዩ አገሮች የኅብረት አገር ለመሆን የመፈለግን ጉዳይ በየአገራቸው ሕዝብ ካስወሰኑ በኋላ ለጋራ ጉባዔ የየአገር ተወካዮቻቸውን ልከው ያቋቋሟት አገር ሳትሆን፣ ፊትም የነበረች ግን በሕገ መንግሥት ጉባዔ ነባር የግንኙነትና የአወቃቀር መሠረቷን ቀይራ የቀጠለች አገር ነች፡፡ 

 ‹‹ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል” ወይስ “እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን››?

‹‹እኔ በአንድ ወቅት በፈጸምኩት ወንጀል ምክንያት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶብኝ ቅጣቴን በመፈጸም ላይ ነኝ፡፡ የዕድሜ ልክ እስራት ፍርደኛ መሆኔ ግን በማረሚያ ቤቱ ውስጥ የማያቸውን የአስተዳደር ችግሮችም ሆነ በታራሚዎች ዘንድ የማየውን ግድፈት ከመናገር አያስቀረኝም፡፡

ከአሥር ቀናት አሰልቺ ንዝንዝና ጭቅጭቅ የበዛበት የአዲስ ዓመት ረዥም ‹‹ሽግግር›› በኋላ እነሆ 2010 ዓ.ም. ውስጥ ገብተናል፡፡ የአዲሱን የ2010 ዓ.ም. መዳረሻ ሁለት ሳምንታት የንዝንዝ ጊዜ ያደገው ባለፈው ሳምንት እንዳመላከትኩት፣ ሕዝባዊ በዓላትን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ የማድረግ ያልተላቀቀን ክፉ ልምድ ነው፡፡ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ የመንግሥት ያለስፍራውና ያለቦታው መግባት ነው፡፡

አገራችን የምታከብራቸው የሕዝብ በዓላት በሕግ የታወጁና በዓለምም የታወቁ ናቸው፡፡ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የግል ድርጅቶችና የንግድ ሱቆች፣ ባንኮችም ጭምር ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ የሚሆኑበት በመሆኑ በተለይ በውጭ ታዋቂ ያደርጋቸዋል፡፡

መንግሥት ገዢው ፓርቲ ውስጥ የደረሰበትን ‹ ‹ቦናፖርታዊ መበስበስ›› እና የመሰንጠቅ አደጋ ከተቆጣጠረ በኋላ በ1993 ዓ.ም. ያወጣው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሕግ፣ ‹‹ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለመሸከም የማይፈልግና ይህንኑ በብቃት ለመዋጋት ዝግጁ የሆነ ኅብረተሰብ መፍጠር አስፈላጊ›› ነው    

እህል በወፍጮ እንደሚከካ፣ እንጨት በመላጊያ እንደሚላግና እንደሚፈቀፈቅ የሰው ልጅም እንደዚህ ሊደረግ ይችላል፡፡ የሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ዜጎቹን ሳይመካከሩ ተመሳሳይ ኦፊሴላዊ ባህርይ እንዲይዙ (ሳይስቁ የሚስቁ፣ ሳያለቅሱ እንባ የሚያወጡ) አድርጎ ፈቅፍቋቸዋል፣ ከክቷቸዋል፡፡

እውነታ በየጊዜው የሚያደረገውን ለውጥ እያነበቡ አቋማቸውንና ተግባራቸውን ድርቅርቅ የሚያደርጉ የፖለቲካ አካላት በገዢዎችም በተገዢዎችም በኩል መኖራቸው ለዓለማችንም ሆነ ለአገራችን እንግዳ አይደለም፡፡

Pages