አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በወጣው መግለጫ፣ በክልሉ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት በሕዝቦችና በመንግሥት መካከል ጥርጣሬና ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ ያሉ አካላት ለሕግ እንደሚቀርቡ አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመንግሥት የተፈቀዱ ከቀረጥ ነፃ መብቶች ማስፈጸሚያ መምርያ ኃላፊ ዓለም ፀሐይ ግርማይ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ሲመረመሩ ከቆዩ በኋላ፣ ጉዳዩን እያየው የነበረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት የ50,000 ብር የዋስትና መብት ቢፈቅድላቸውም ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ፡፡

ማክሰኞ መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በተከበረው የደመራ በዓል ላይ የተገኙት የህንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ሲሪያን ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፣ በኢትዮጵያ አቻቸው በአቡነ ማትያስ ግብዣ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ከልብ እንዳስደሰታቸው ተናገሩ፡፡

በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ትልልቅ የሚባሉ የግንባታ ሥራዎችን በማከናወን የሚታወቀው በቻይና መንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደረው ቻይና ኮንስትራክሽን ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን (ሲሲሲሲ)፣ በግሉ እየገነባ ያለውን የኢንዱስትሪ ፓርክ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በዚህ ዓመት ዲቪ ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት የነበረ ቢሆንም የአሜሪካ ኤምባሲ እ.አ.አ. የ2019 የዲቪ ምዝገባ እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 3 ቀን 2017 እንደሚጀመር አስታወቀ፡፡ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስደትና በስደተኞች ላይ ባላቸው አቋም የተነሳ በዚህ ዓመት ዲቪ ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ነበር፡፡

በቅርቡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት፣ የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው፡፡ ኮንፈረንሱን ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

  • የኬንያ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ተጠይቋል
  • መፍትሔ ካልተገኘ ስኳሩ ወደ ወንጂ ሊመለስ ይችላል

ከአንድ ወር በፊት ወደ ኬንያ ኤክስፖርት ተደረገ የተባለው ስኳር የኢትዮጵያ ሞያሌ ድንበርን አለማለፉን፣ የስኳር ምርቱን የገዛው መቀመጫውን በዱባይ ያደረገው ኩባንያ ችግሩን መፍታት አለመቻሉን ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች አመለከቱ፡፡

  • ለሁለቱም ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ መፈጸሙ ተገልጿል
  • ሳትኮንና ሀዚ አይአይ ሥራ ተቋራጮች በክሱ ተካተዋል

ከሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው በከረሙት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሰባት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገምሹ በየነ (በሌሉበት) እና በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ማሞ (በሌሉበት) ላይ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

Pages