አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

  ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ነኝ የሚለው አዲስ ቴሌቪዥን መስከረም 13 ቀን 2010 ዓ.ም. በዕለታዊ የዜና ማስታወሻ ፕሮግራሙ በምሥልና በጽሑፍ አስደግፎ ካቀረባቸው ዜናዎች መካከል “የጂማ፣ የባህር ዳርና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህራን የትምህርት ልቀት ማዕከላት እንዲሆኑ ተመረጡ” የሚለው አንዱ ነበር፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ችግሮች የሚገጥሙን እኛ እንዲሆንልን የምንፈልገውን ነገር ለማድረግ የሌሎችን ሐሳብም ሆነ ፍላጎት ሳንረዳ፤ ብንረዳም ከቁም ነገር ባለመቁጠር እንደዋዛ ወደ ጎን በመግፋት ነው፡፡ የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ደግሞ ሁልጊዜ ችግር ማስከተሉ አይቀርም፡፡ የደረሰውን ችግር ለማረም ብንፈልግ ግን የሚከፈለው ዋጋ እጅግ የሚጎዳ ነው፡፡ ለእነዚህ ማሳያ የሚሆኑ ጥቂት አብነቶችን ብቻ እንይ፡፡

የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከደመነፍሳዊ ጉዞው ነቅቶ በስልት መጓዝ ወደሚችልበት መንገድ በመግባትና ዓለም አቀፉን የእግር ኳስ ቅኝት መሠረት በማድረግ  መሥራትና መትጋት ካልጀመረ፣ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ትንሳዔ መቼም ቢሆን ሊቃረብ እንደማይችል ለመናገር ነብይ መሆንን አይጠይቅም፡፡

አዲሱ ነገር ባሮጌው ትናንት ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ የተፀነሰውን ዘረኝነት ደካማ የሥራ ባህል ጭፍን አክራሪነት፣ በሥልጣን መባለግ በረብ የለሽ ልማድ መተብተብ፣ ከድንቁርና የማይተናነሰውን የስሜታዊነት ጽንስ ሳናመክን የነገን ብርሃን በተስፋ መጠበቅ ከምኞት ያለፈ ፋይዳ የለውም ፡፡

የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ስለ ሥልጠና፣ ስብሰባና ሙስና ምንነት ትንታኔ ለማቅረብ ሳይሆን፣ በእነዚህ ምክንያት ለሚባክኑ የሕዝብ ገንዘቦችና ንብረቶች የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶችና ሹመኞች የተዝረከረከውን አሠራር በማጤን የሕግ ሥርዓት እንደዲዘረጉለት (ልግጓም) እንዲያበጁለት ለመነሻ የሚሆን መረጃ ለማቀበል ነው፡፡

ከቅርብ ቀናት በፊት በአገሪቱ ለአሥር ወራት ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱ ይታወሳል፡፡ ከዕረፍት ተመልሶ አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በአብዛኛው የአገሪቷ ቦታዎች በአንፃራዊነት ሰላም በመስፈኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወስኗል፡፡ 

ከቅርብ ቀናት በፊት በአገሪቱ ለአሥር ወራት ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱ ይታወሳል፡፡ ከዕረፍት ተመልሶ አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በአብዛኛው የአገሪቷ ቦታዎች በአንፃራዊነት ሰላም በመስፈኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወስኗል፡፡   

Pages