አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ሰላም! ሰላም! ስንሞት በፎቶ እንጂ በባንክ አካውታችን የሚለቀስልን ይመስል ገንዘብ ላይ እኝ ብለን ልንሞት ነው አሉ። ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር የምንሸጋገረው እንግዲህ በዚህ አያያዛችን መሆኑ ነው።

ሰላም! ሰላም! ሰው ዘንድሮ ምን እንደበላ ወይ ምን እንዳበሉት አላውቅም፣ ከራስ በላይ አዋቂ ሆኗል። ለራስ የሚያውቅ ጠፍቶ ምክር በዱላ በሆነበት አገር ሰው ለመምከር የሚያዘው ሠልፍ የታክሲ ሠልፍ ያስንቃል።

ሰላም! ሰላም! “የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ የኢትዮጵያን የሰሜን ተራሮች ተነስታችሁ ወደ ህንድ ውቅያኖስ ስጠሙ ብላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ፤” ብለው ማስተማር ቢጀምሩስ ቴክሳሶች? ሲያሻን ተራራ እያንቀጠቀጥን ሲያሻን ደግሞ ተራራው እየተንቀጠቀጠብን የእኛ መጨረሻ እንዲያው ምን እንደሚሆን ዝም ብሎ ማየት ነው። 

ሰላም! ሰላም! ‹‹እኔን ያሰኘኝ ፍቺው ፍቺው...›› አለች አሉ ዘፋኟ፡፡ ገር ልብ ያለው ሰው ድሮም መጨረሻው ፍቺ እንጂ አብሮነት አይሆን። ዋናው አያችሁ ማጠንጠኛው ነው። ገር አገር ሲያጣም ዕጣው ተመሳሳይ ነው። 

ሰላም! ሰላም! መኖር መቼም ደግ ነው። በመቆየት ብዙ ዓየን። ያደላቸው ደግሞ ላላዩት ጭምር ያያሉ። እሱን ‘ፀጋ’ ብሎ ማለፍ ሳይሻል አይቀርም። የምር ግን እያዩ የማያዩ፣ እየሰሙ የማይሰሙ ሰዎች ቁጥር አልበዛባችሁም?

ሰላም! ሰላም! “ይህ ሕይወት ካለፈው የቀጠለ ነው። አሁን የምትኖረው ያለምከውን ነው፤” አለኝ አንዱ በቀደም። አንዱ የምለው ወድጄ እንዳይመስላችሁ። አንድ አንድ እያልን ካልነጣጠልነው የዘንድሮ ቅዠት ተደራጅቶ ገና ጉድ ይሠራናል። 

ሰላም! ሰላም! ‹የታሰረን አንጀት ያላሰረ አይፈታ› እያለ የሚዘፍን አልበዛባችሁም? መቼም ‹ማታ ማታ› እያሉ ምሽት ተኮር ዘፈን ከማብዛት የሚሻል ይመስላል። ካልተሸራተትን ማለቴ ነው። ብንንሸራተትም መንሸራተት በእኛ አልተጀመረም።  

ሰላም! ሰላም! ሩጫው እንዴት ይዟችኋል? ብርዱማ እንደምታዩት ዙር ይደርባል። መደረቡ ሳያንስ አገርና ስሙን በዓለም ያስጠራል። ግን ይኼም አይገርመንም አሉ። “እንዴት?” ብል “መደረብ ብርቅ ነው እንዴ? ይኼ ሁሉ ሰው ደራቢ እኮ ነው።

ሰላም! ሰላም! ሰሞኑን መርካቶ እግር አበዛሁና የምሠራው ሳጣ ጥያቄ ፈጠርኩ። ሥራ ፈጠራ ከብዷላ። ለአንዳንድ የረጅም ጊዜ ጥያቄዎቼ መልስ የማገኝበት መንገድ በአብዛኛው አስገራሚ ሆኖ አገኘዋለሁ።

ሰላም! ሰላም! እንዴት ነው ሰሞኑን ቅፅበታዊ እብደቶች አልበዙባችሁም? ግብር በግምት እንደ መብረቅ እየባረቀብን እንዳትሉኝ ብቻ? ክፍት የሥራ ቦታ እብደትና ልመና ብቻ የሆኑ እስኪመስለን ድረስ ጎዳናው እያደር የከሰሩ ዜጎች ይበዙበት ጀምሯል።

Pages