አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

በመቐለ ከተማ የመስቀል በዓል በሚከበርበት ጮምአ ላይ የተተከለው 52 ሜትር መስቀል መስከረም 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተመርቋል፡፡ 

የመጨረሻውን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (1923-1967) ከሥልጣን ያነሣው የጦር ኃይሎች የፖሊስ ሠራዊትና የብሔራዊ ጦር አስተባባሪ ደርግ፤ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ በመባል ሥልጣኑን ሲቆናጠጥ፣ ቆይቶም የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ሆኖ እስከ 1979 ዓ.ም.፣ በይቀጥላልም የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ሆኖ እስከ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢሕአዴግ እስካስወገደው ድረስ ዘልቋል፡፡ 

በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሕንዳውያን ከ62 ዓመት በፊት በ1948 ዓ.ም. ያሠሩትና ሲኒማ አምፒር አጠገብ ይገኝ የነበረው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ (1923-1967) ሐውልት! በመስከረም 1967 ዓ.ም. በዘመነ ደርግ ፈርሶ ከተጣለ በኋላ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም አፀድ ውስጥ ያለ አንበሶቹ እንደነገሩ የቆመ፡፡ 

የዓመቱ 359ኛ ቀን ዓመቱ ሊያበቃ 6 ቀን በቀረበት ነሐሴ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በአብዛኞቹ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በእኩለ ቀን (ስድስት ሰዓት ግድም) አካባቢ ጀምሮ የጣለው ከባድ ዝናብ የአዲስ አበባን ጎዳናዎች በጎርፍ እንዲጥለቀለቁ አድርጓል፡፡

በ1950ዎቹ መጀመርያ ጫማ አስጠራጊ አዲስ አበቤዎች በፒያሳ ሲኒማ ኢትዮጵያ አካባቢ 

መሰንበቻውን ለንደን ለአሥር ቀናት ባስተናገደችው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተፈጠሩት አስገራሚ ክስተቶች አንዱ በ3000 ሜትር መሠናክል የሴቶች ውድድር ላይ ነሐሴ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. የታየው ነበር፡፡

በእንግሊዝ መዲና ለንደን እየተካሄደ ባለው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሐምሌ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. 10 ሺሕ ሜትር ውድድር አልማዝ አያና ያሸነፈችው፣ ዓምና በሪዮ ኦሊምፒክ እንዳደረገችውና እንደለመደችው ከግማሽ በላይ የሆነውን ርቀት ብቻዋን በመሮጥ ነበር፡፡

Pages