አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ሑድ ነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከአገሪቱና ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት ጋር የተወያዩት የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ፣ ከሰሜን ኮሪያ የኑክሌርና የሚሳይል ጥቃት ጀምሮ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በሚታዩት የፀጥታ ሥጋቶች ላይ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የሚስማማ አቋም እንዳላት አስታወቁ፡፡

  • ተቃዋሚዎች ለምርጫ ሕጉ ድርድር ዝግጅት እያደረጉ ነው

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተቋማዊ ቅርፅ ላይ ማሻሻያ ለማድረግና የምርጫ ኮሚሽን ሆኖ እንዲቋቋም ጥናት እያከናወነ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ግንኙነት በማንኛውም መሥፈርት እጅግ የተወሳሰበ ነው፡፡ ለዘመናት በእርስ በርስ ጦርነት፣ ግጭትና ፖለቲካ ፍትጊያ ውስጥ  አልፈዋል፡፡ አልፎ አልፎም ሁለት ሆነው በማበር አንዱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያሴሩበት አጋጣሚም ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

የሙስና ወንጀል ተግባራት ጋር ተያይዞ መንግሥት እየወሰደ ያለው ዕርምጃ የዘገየ አለመሆኑንና የባለሥልጣን ከለላ ያላቸው አይነኩም የሚለውን አመለካከት እንደማይቀበሉት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡ መንግሥት ከአሁን በኋላ በአገሪቱ አለመረጋጋትን የሚያስከትሉ ክስተቶችን እንደማይታገስም አስጠንቅቀዋል፡፡

የተከሰሱበት የሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ ወደ ወንጀል ሕግ ተቀይሮ እንዲከላከሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው አቶ በቀለ ገርባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳን በመከላከያ ምስክርነት በመቁጠራቸው ባለሥልጣናቱ እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

Pages