አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የአማራና የቅማንት ሕዝቦች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች በማኀበረሰቦቹ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ አስተዳደር ለማቋቋም ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ በተወሰነው መሠረት፣ መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ወሰነ።

  • በሁለት ወራት ከ1.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የዕርዳታ እህል ተከፋፍሏል

በዚህ ዓመት በተካሄደው የበልግ ወቅት ጥናት መሠረት፣ በአሁኑ ወቅት ከ8.5 ሚሊዮን በላይ የድርቅ ተጎጂዎች ከሐምሌ 2009 ዓ.ም. እስከ ታኅሳስ 2010 ዓ.ም. የሚያቆይ የምግብና ሌሎች የዕለት ደራሽ ዕርዳታዎችን ለማቅረብ 487.7 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የፌዴራል ባለ በጀት መሥሪያ ቤቶች በቅርቡ ያሠራጨውን የበጀት ወጪ ቅነሳ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው፣ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ እንዲያቀርቡ አዘዘ፡፡ በመመርያው መሠረት በርካታ አላስፈላጊ ወጪዎችን እንዲቀንሱ ጠበቅ ያሉ ክልከላዎች ተደርገዋል፡፡          

‹‹በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ፖለቲካ መሥራት ይቻላል? ሕዝቡንና አገሪቷንስ እንዴት ወደ ሰላም ማምጣት ይቻላል?›› ሲሉ ጥያቄ አዘል አስተያየታቸውን ሰሞኑን ለሪፖርተር የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ የሺዋስ አሰፋ ናቸው፡፡ 

  • በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ድጋሚ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለማየሁ ጉጆ 500,000 ብር ጉቦ በማቀባበል የተጠረጠሩት አቶ ኢዮብ በልሁ፣ በቁጥጥር ሥር ውለው ነሐሴ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመንግሥት የተሰጡ ከቀረጥ ነፃ መብቶች ማስፈጸሚያ መምርያ ኃላፊ፣ በተጠረጠሩበት ከአሥር ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል በድጋሚ 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው፡፡

በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር እሑድ ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በመብራት ኃይል አዳራሽ ውይይት ለማድረግ ያስገቡትን የዕውቅና ጥያቄ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ባለመስጠቱ ምክንያት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) ዕቅዳቸውን መሰረዛቸውን አስታወቁ፡፡

Pages