አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

​​​​​​​ዓቃቤ ሕግ በመንግሥት ላይ ጉዳት በማድረስ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ተጠርጥረው የታሰሩትን አቶ ሳምሶን ወንድሙንና አቶ በቀለ ባልቻን ከእስር ለቀቀ፡፡ ዓቃቤ ሕግ ግን ፍርድ ቤቱን ሳያስፈቅድ ግለሰቦቹን በመልቀቁ፣ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን ተቃውሞታል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም. መግቢያ ድረስ በአገሪቱ እየተከሰተ ያለው ተቃውሞና ግጭት ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ወደ ሥልጣን ከመጣ ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ በአገሪቱ ለረጅም ጊዜ ተቃውሞና ግጭት ሲከሰት ይኼ የመጀመሪያው እንደሆነ፣ የፖለቲካ ተንታኞች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

የዶላር ዕጥረት የመገጣጠም አቅሙን እንደገደበው ገልጿል

አዳዲስ ሞዴሎቹን ለኢትዮጵያ ገበያ ለማስተዋወቅ ሐሳብ አለው

የሊፋን ኢንዱስትሪ ግሩፕ አካል የሆነው ሊፋን ሞተርስ ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ ያለውን እንቅስቃሴ ለማሻሻል እንዲረዳው ዋና መሥሪያ ቤት ለመገንባት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

 ከመሬት በላይ 107 ሜትር ከፍታ ባለው የሕንፃ አናት ላይ እንገኛለን፡፡ ከሕንፃው አናት ላይ በመሆን አዲስ አበባን በሁሉም አቅጣጫ መቃኘት ይቻላል፡፡ ከአዲስ አበባ ብሔራዊ ስቴዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው አዲሱ ሕንፃ በከተማው ከበቀሉ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች አንዱ ሲሆን፣ ሕንፃውን ያስገነባው የወጋገን ባንክ ኃላፊዎችም የከተማውን ረጅም ሕንፃ ዕውን እንዳደረጉ ይናገራሉ፡፡

የአገሪቱ የወተት ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለያዩ ችግሮች እንደሚታዩ ሲገለጽ ሰነባብቷል፡፡ በወተት አቅራቢዎችና በወተት አቀነባባሪዎች መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ጤና ማጣቱ በወተት አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው፡፡

በ2009 በጀት ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ አዋጆችን አፅድቋል፡፡ እንደሚፀድቁ የሚጠበቁም ነበሩ፡፡ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረቡ አዳዲስ ሕጎች እንደነበሩም እናስታውሳለን፡፡ ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል የተባሉ ሕጎችም በይደር ታልፈዋል፡፡

አቶ አየልኝ ሙሉዓለም፣ የቀድሞው ሰሜን የአሁኑ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

በ2008 ዓ.ም. ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲነሳባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል አንዱ ሰሜን ጎንደር ዞን ነው፡፡ በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው ሁከት ከስድስት መቶ በላይ ዜጎች ሕይወት መጥፋቱና ንብረት መውደሙ ይታወሳል፡፡

ችግሮቹ?

በገነት ዓለሙ

“ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ” የተሰኘችው ኢትዮጵያ ነፃ የሆኑ የተለያዩ አገሮች የኅብረት አገር ለመሆን የመፈለግን ጉዳይ በየአገራቸው ሕዝብ ካስወሰኑ በኋላ ለጋራ ጉባዔ የየአገር ተወካዮቻቸውን ልከው ያቋቋሟት አገር ሳትሆን፣ ፊትም የነበረች ግን በሕገ መንግሥት ጉባዔ ነባር የግንኙነትና የአወቃቀር መሠረቷን ቀይራ የቀጠለች አገር ነች፡፡ 

በዳንኤል አረጋዊ ኃይሉ

አዲስ ዓመት ሲመጣ በዓመቱ ልናከናውናቸው የምንሻቸውን ነገሮችን ማቀድ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ ከአዲስ ዓመት መባቻ ጀምሮ ይህንን ልምዳችንን ከግምት ያስገቡ፣ በዕቅድ መመራትን ማዕከል ያደረጉ፣ የተለያዩ ዝግጅቶች በሬዲዮ ስናደምጥና በቲቪ ስንመለከት ከርመናል፡፡ 

Pages