አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ የሕዝብ መፈናቀልን ለማስቆም ቃል ቢገባም፣ በተለይ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የመጠለያ ጣቢያዎችን አጨናንቀዋል፡፡ እስካለፈው ሳምንት መጀመርያ ድረስም ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 67 ሺሕ እንደደረሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር ኢትዮጵያ መምጣታቸውንና ሥራ መጀመራቸውን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ ኤምባሲው ዓርብ መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ አምባሳደሩ ለኢትዮጵያዊያን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሰላም! ሰላም! ስንሞት በፎቶ እንጂ በባንክ አካውታችን የሚለቀስልን ይመስል ገንዘብ ላይ እኝ ብለን ልንሞት ነው አሉ። ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር የምንሸጋገረው እንግዲህ በዚህ አያያዛችን መሆኑ ነው።

‹‹በዕዳ የተያዘ ሕዝብ›› ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የጋዜጠኛ፣ ጸሐፊ ታሪክና የፖለቲካ ተንታኝ ሙሉጌታ ሉሌ በጦቢያና ልሣነ ሕዝብ መጽሔቶች ያስነበባቸውን ጽሑፎች የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡

መስከረም 17 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ ሲከበር ከአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ 2 ሺሕ አገልጋዮች ፅናፅን፣ መቋሚያና ከበሮ ይዘው በዓሉን በወረብ አድምቀውታል፡፡ ምዕመኑም ጧፍ በመለኮስ የደመራውን ምሽት አስውበውታል፡፡ በዕለቱ የውጭ አገር ዜጎችም ነጠላቸውን ጣል አድርገው ጧፍ አብርተው ታይተዋል

ከነፍሳት ወገን የሆነችው ዋዥምቢት፣ ዋዝንቢት ሌላው መጠርያ ስሟ ነው፡፡ በየኔታ ደስታ ተክወልድ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት እንደተገለጸው፣ ዋዥምቢት ጥቁር ትል እህል አጥፊ ናት፡፡ የተለያዩ ቀለም እንዳላትም ይታወቃል፡፡ አንዱ አረንጓዴ ዓይነትማ ነው፡፡

Pages