አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

​​​​​​​ዓቃቤ ሕግ በመንግሥት ላይ ጉዳት በማድረስ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ተጠርጥረው የታሰሩትን አቶ ሳምሶን ወንድሙንና አቶ በቀለ ባልቻን ከእስር ለቀቀ፡፡ ዓቃቤ ሕግ ግን ፍርድ ቤቱን ሳያስፈቅድ ግለሰቦቹን በመልቀቁ፣ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን ተቃውሞታል፡፡

  • ባቱ ኮንስትራክሽንና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ተቋራጭ ያላግባብ ጥቅም ማግኘታቸው ተገልጿል

በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በተለያዩ ጊዜያት ሥራ አስኪያጅና በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃ ላይ የነበሩ ዘጠኝ ተከሳሾች፣ ከባለሀብቶች ጋር በመመሳጠርና ጥቅም ለማግኘት በማሰብ፣ ያላግባብ ክፍያ በመፈጸማቸው በፋብሪካው ላይ በድምሩ ከ96.9 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

  • በብድር ከተገኘ 10.1 ቢሊዮን ብር ላይ 15.9 ሚሊዮን ብር ኮሚሽን መከፈሉ ተገልጿል

የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክትን በጨረታ አወዳድሮ መስጠት ሲገባቸው፣ በሕገወጥ መንገድ በደላሎች አማካይነት ለቀረበው ጃንዚ ጃንግሊያን ኢንተርናሽናል ኢንጂነሪንግ ካምፓኒ በ12,119,913,986 ብር በመስጠት፣ በመንግሥትና ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል

  • አንድ ተጠርጣሪ በ20 ሺሕ ብር ዋስ ሲለቀቁ ሦስት ተጠርጣሪዎች  ተቀጥረዋል

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከፍተኛ ኃላፊዎች ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀምና በመመሳጠር ጥቅም ለማግኘትና ለማስገኘት አስበው፣ ለመንገድ ግንባታዎችና ጥራቱን ላልጠበቀ የአስፋልት ግዥ ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈጸም በመንግሥትና ሕዝብ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሐሙስ መስከረም 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በመሠረተባቸው ሁለት ክሶች አስታወቀ፡፡

  • ሦስት ተጠርጣሪዎች የዓቃቤ ሕግ ምስክር ለመሆን በመስማማታቸው ተለቀቁ

 የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎችና የግል ተቋም  ሠራተኞች በጥቅም በመመሳጠር፣ ሚኒስቴሩ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት ግንባታ ለመዘርጋትና የአገሪቱን የፋይናንስ አስተዳደር መዋቅሮችን በዘመናዊ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥርዓት ለማስተሳሰር ወጥቶ የነበረውን ጨረታ ማሸነፍ ካልቻለ ድርጅት ጋር፣ በሕገወጥ መንገድ የ501,750,722 ብር ውል ፈጽመዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ መሠረተባቸው፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመንግሥት የተፈቀዱ ከቀረጥ ነፃ መብቶች ማስፈጸሚያ መምርያ ኃላፊ ዓለም ፀሐይ ግርማይ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ሲመረመሩ ከቆዩ በኋላ፣ ጉዳዩን እያየው የነበረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት የ50,000 ብር የዋስትና መብት ቢፈቅድላቸውም ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ፡፡

  • ለሁለቱም ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ መፈጸሙ ተገልጿል
  • ሳትኮንና ሀዚ አይአይ ሥራ ተቋራጮች በክሱ ተካተዋል

ከሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው በከረሙት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሰባት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገምሹ በየነ (በሌሉበት) እና በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ማሞ (በሌሉበት) ላይ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

  • በገንዘብ ሚኒስቴርና በስኳር ኮርፖሬሽን ተጠርጣሪዎች ላይ የመጨረሻ ቀጠሮ ተሰጠ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት፣ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዓቃቢያነ ሕግ ላይ የመጨረሻ የተግሳጽ ቅጣት ሰጠ፡፡

የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያላግባብ በመገልገልና ከሥልጣቸው በላይ በመጠቀም ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግሥትና ሕዝብ ሀብት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ፣ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ሰባት ኃላፊዎችና አንድ ባለሀብት ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

ኢትዮጵያ በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ የምታገኘውን ገቢና ወጪ በአግባቡ መጠቀም ሲገባቸው ኃላፊነታቸውን ያላግባብ በመጠቀም፣ በሕዝብና በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ተጠርጥረው በምርመራ ላይ የሚገኙት የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊዎች፣ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

Pages