አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ፍሬከናፍር

‹‹ለዘመናት የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩና ማራኪ የማይዳሰሱ ቅርሶቻቸውን ሰላምን ለመገንባት ተጠቅመውበታል፡፡ ይህንን አንዳቸው ሌላቸውን የመገንዘብና የመቻቻል ባህል በዓለም ላይ በርካታ ሕዝቦችን እየተፈታተነ ያለውን አለመግባባት  ለመግታት ልናውለው እንችላለን፡፡››

የተባበሩት መንግሥታት ቴክኒካል ኤክስፐርት ዶ/ር ኩሱም ጎፔል፣ ከካሽሚር ኦብዘርቨር ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተቀነጨበ፡፡ ዶ/ር ኩሱም የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን ለሰላምና መረጋጋት በማዋል ረገድ ከአፍሪካ ቀንድ አገሮች መካከል የኢትዮጵያን ቅርሶች እንደ ማስረጃ ይጠቅሳሉ፡፡ እንደ ማሳያም፣ ይህን መሰል አገር በቀል ዕውቀት ያለውን ሚና ከግምት በማስገባትም የኦሮሞ ሕዝብ ማኅበራዊና ባህላዊ ሥርዓት የሆነው ገዳ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) መዝገብ ላይ አምና መስፈሩ ይጠቀሳል፡፡