አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

‹‹አዲሱ ትውልድ የይድነቃቸው ተሰማን አርአያ እንዲከተልና እግር ኳሱን ለማሳደግ አብሬ ለመሥራት ፍላጎት አለኝ፡፡››

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ በኢትዮጵያ ባደረጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸው የተናገሩት፡፡ ካፍን በመምራት በእግር ኳሱ አሻራ ያሳረፉትን አቶ ይድነቃቸው ተሰማ እውቅና እንዲሰጣቸው ጥረት አደርጋለሁ ያሉት የካፍ ፕሬዚዳንት፣ በዚህ ሳምን መጀመርያ በነበራቸው ቆይታ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚ፣ የካፍ አካዴሚንና በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው ብሔራዊው አደይ አበባ ስታዲየም የግንባታ ሒደትን ጎብኝተዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር በተወያዩበት ጊዜም በመንግሥት አማካይነት እየተከናወኑ ያሉትን የስታዲየሞች ግንባታ አድንቀው በወጣቶች ላይ ትኩረት በመስጠት መሥራት እንደሚገባ ሳያሰምሩበት አላለፉም፡፡ ማዳጋስካራዊ አህመድ አህመድ ከመንፈቅ በፊት በአዲስ አበባው የካፍ ጉባኤ በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለሦስት አሠርታት ግድም የመሩትን ካሜሩናዊውን ኢሳ ሃያቱን በከፍተኛ ድምፅ ብልጫ አሸንፈው መንበሩን መረከባቸው ይታወሳል።