አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

 ለመደማመጥ ሰከን ብሎ መነጋገር ያስፈልጋል፡፡ ስክነትና ትዕግሥት በሌለበት ከመጯጯህ የዘለለ ቁም ነገር አይገኝም፡፡ አስተሳሰቤ ተሸናፊ ይሆንብኛል ወይም በዓይኔ እንኳ ማየት የማልፈልገው ሰው ሊሞግተኝ ይችላል ተብሎ ከውይይት መሸሽ ተቀባይነት የለውም፡፡ በግለሰብ ደረጃም ሆነ በመንግሥት የዕለት ተዕለት ሥራ፣ በፓርቲ ፖለቲካም ሆነ በተለያዩ ጉዳዮች መነጋገር ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡

አገርን ከቀውስ ወደ ቀውስ በማሸጋገር ትርምስ መፍጠር አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ በዜጎች ውድ ሕይወት ላይ መቆመር ያሳዝናል፡፡ የኢትዮጵያዊነት የጋራ መገለጫ የሆኑት ጨዋነት፣ አስተዋይነትና አርቆ አሳቢነት ወደ ጎን እየተገፉ ግንፍልተኝነትና ግትርነት እየገነኑ ነው፡፡ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ደም አፋሳሽ ግጭት በተቻለ መጠን በፍጥነት ካልቆመ፣ ሕዝብን ለዕልቂት አገርን ደግሞ ለማያባራ ጦርነት ይዳርጋል፡፡

በአዲሱ ዓመት ከፀብና ከጥላቻ የፀዳች ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር ማለት አለብን፡፡ ይህ የመልካም ምኞት መግለጫ አገራቸውን የሚወዱ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ይሆን ዘንድ በብሩህ ተስፋ መነጋገር ይገባል፡

አስመሳይነት የአድርባዮች መገለጫ ነው፡፡ በዚህ ድርጊት የሚታወቁ ሰዎች ደግሞ በሞራልና ሥነ ምግባር ዝቅጠት፣ በራስ ወዳድነት፣ በማይገባ ጥቅም ፈላጊነት፣ በዓላማ ቢስነት፣ በብቃት የለሽነትና በሕገወጥነት ተወዳዳሪ የሌላቸው ናቸው፡፡

Pages