አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
  • የተጨዋቾች የዝውውር ክፍያና አሠራር ክትትል እየተደረገበት መሆኑም ተነግሯል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሚያከናውናቸው ዋነኛ ተግባራት አንዱ አዲስ የውድድር ዓመት ሲጀመር የድልድል ዕጣ ማውጣት ይጠቀሳል፡፡ በዚሁ ፕሮግራም ላይ ያለፈውን ዓመት የዘርፉን እንስቃሴዎች መቃኘት፣ የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መገምገም ላይ ያተኩራል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰው ልጅን ቀልብ መግዛት ከቻሉ ስፖርቶች ውስጥ እግር ኳስ ተጠቃሽ ነው፡፡ እግር ኳስ በተለይም አሁን አሁን ማኅበረሰብን፣ ፖለቲካን እንዲሁም የአንድ አገር የኢኮኖሚ ዕድገት የመለወጥ ትልቅ አቅም እንዳለው ይታመናል፡፡ 

አቶ ተድላ ዳኛቸው፣ በስፖርት ማኔጅመንት የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን በመሥራት ላይ የሚገኙ

እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ጨምሮ 26 ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ማለት በሚያስችል መልኩ ስፖርቱ በተለይም በአሁኑ ወቅት ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ አኳያ አደረጃጀታቸውን ጨምሮ በተለያዩ ሳንካ ተይዞ እንደሚገኝ የስፖርቱ ሙያተኞች ይናገራሉ፡

  • የ2010 የውድድር ፕሮግራም በክረምቱ ምክንያት መራዘሙ ተነግሯል

 ከአንድ ዓመት የፕሪሚየር ሊግ ቆይታ በኋላ በ2009 ዓ.ም. ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደው የጅማ  አባቡና እግር ኳስ ክለብ፣ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ያቀረበው አቤታቱ ምላሽ ያላገኘው በፌዴሬሽኑ ቸልተኝነት እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡ ጉዳዩ በፌዴራል ፖሊስ የምርመራ ቢሮ እጅ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

  ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በየውድድር አውድማ ታላላቅ ስፖርታዊ ድሎችን ባስመዘገቡ ቁጥር ብሔራዊ ደስታና ፈንጠዝያው ደምቆ የሚጎላው ወደ አገር ቤት ሲመለሱ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ሕዝብ ባለፉበት አደባባይና ጎዳና እየተጋፋ የሚመለከታቸው፣ በጩኸትና በእልልታ እያጀበ የሚከተላቸው ባለ ድል አትሌቶች አቀባበል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደበዘዘ መጥቶ ነበር፡፡

  • በሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ የቻይና ቆይታውን አጠናቆ ተመልሷል

ከዓለም ኃያል አገሮች አንዷ የሆነችው ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር በስፖርቱም ለመቀጠል ፍላጎት ማሳየቷ ተገለጸ፡፡ በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ርስቱ ይርዳው የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት አድርጎ ተመልሷል፡፡ ሁለቱ አገሮች በስፖርቱ በትብብር መሥራት የሚችሉበት መግባቢያ ሰነድ በቅርቡ ይፈራረማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡

  • አገር አቀፉ የስፖርት ፖሊሲ ክለሳ ሳይደረግለት ሁለት አሠርታት አስቆጥሯል

 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ሌሎችም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በፖሊሲ አፈጻጸም ክፍተት ለውድቀት እየተጋለጡ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ለዚህ በዋናነት ምክንያት ተደርጎ የሚጠቀሰው ደግሞ በ1990ዎቹ መጀመርያ በአገር አቀፍ ደረጃ ሥራ ላይ እንዲውል የተደረገው የስፖርት ፖሊሲ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የማሻሻያ ክለሳ ሳይደረግለት ሁለት አሠርታትን ማስቆጠሩ እንደሆነ እየተጠቀሰ ይገኛል፡፡

Pages