አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ሙስና የግል ሴክተሩም እንደሚነካ መቼም ታውቂያለሽ፡፡
እኔን አይመለከተኝም አልኩህ፡፡
አሁን ደግሞ ዋና ትኩረትቸው በባለሥልጣናት ዙሪያ ያሉ ሰዎች ላይ ነው፡፡
እያስፈራራኸኝ ነው?
ለማንኛውም ወደ ዱባይ ብትሄጂ ጥሩ ነው፡፡
ስማ እኔ የመጣብኝን እቀበላለሁ፡፡
እስርም ቢሆን?
ለምን እታሰራለሁ?
ያልተገባ ሀብት አካብተሻል ተብለሽ ነዋ፡፡
በቃ እንደሌሎቹ በስሜ ያለን ሀብት ሸጣችሁ ውሰዱት ብሎ መገላገል ነዋ፡፡

·  ክቡር ሚኒስትር አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት?

·  ይቻላል፡፡

·  በዓለም ላይ እንደ ኢሕአዴግ ሥልጠና የሚወድ ድርጅት አለ?

·  እየቀለድክ ነው?

·  እውነቴን ነው እንጂ ከዓመት ዓመት ሥልጠና ላይ ናችሁ እኮ?

·  ሕዝቡን ለማገልገል ሥልጠና ወሳኝ ነው፡፡

·  በእርግጥ ሕዝቡን ለማገልገል ነው ሥልጠና የምትቀመጡት?

·  ታዲያ ለምንድነው?

·  ለአበል ነዋ፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ ወጥተው ቤታቸው ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • ዛሬ መቼም ያልጠበቅኩትን ነገር ነው የሰማሁት፡፡
  • ምንድነው ያልጠበቅሽው ነገር?

Pages