አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
  • መንግሥትና ባለሥልጣናትን እንደሚከስ አስታወቀ

የህንዱ ካሩቱሪ ግሩፕ በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ ችግር ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ሙሉ ለሙሉ ነቅሎ መውጣቱን ባስታወቀ ማግሥት፣ በአገሪቱ ያሉትን ንብረቶች ለማስወጣት እንዲችል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታውን አቀረበ፡፡

  • አንድ ተጠርጣሪ በ20 ሺሕ ብር ዋስ ሲለቀቁ ሦስት ተጠርጣሪዎች  ተቀጥረዋል

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከፍተኛ ኃላፊዎች ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀምና በመመሳጠር ጥቅም ለማግኘትና ለማስገኘት አስበው፣ ለመንገድ ግንባታዎችና ጥራቱን ላልጠበቀ የአስፋልት ግዥ ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈጸም በመንግሥትና ሕዝብ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሐሙስ መስከረም 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በመሠረተባቸው ሁለት ክሶች አስታወቀ፡፡

  • ሦስት ተጠርጣሪዎች የዓቃቤ ሕግ ምስክር ለመሆን በመስማማታቸው ተለቀቁ

 የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎችና የግል ተቋም  ሠራተኞች በጥቅም በመመሳጠር፣ ሚኒስቴሩ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት ግንባታ ለመዘርጋትና የአገሪቱን የፋይናንስ አስተዳደር መዋቅሮችን በዘመናዊ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥርዓት ለማስተሳሰር ወጥቶ የነበረውን ጨረታ ማሸነፍ ካልቻለ ድርጅት ጋር፣ በሕገወጥ መንገድ የ501,750,722 ብር ውል ፈጽመዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ መሠረተባቸው፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር ኢትዮጵያ መምጣታቸውንና ሥራ መጀመራቸውን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ ኤምባሲው ዓርብ መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ አምባሳደሩ ለኢትዮጵያዊያን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Pages