አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፣ ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኃላ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በወጣው መግለጫ፣ በክልሉ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት በሕዝቦችና በመንግሥት መካከል ጥርጣሬና ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ ያሉ አካላት ለሕግ እንደሚቀርቡ አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመንግሥት የተፈቀዱ ከቀረጥ ነፃ መብቶች ማስፈጸሚያ መምርያ ኃላፊ ዓለም ፀሐይ ግርማይ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ሲመረመሩ ከቆዩ በኋላ፣ ጉዳዩን እያየው የነበረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት የ50,000 ብር የዋስትና መብት ቢፈቅድላቸውም ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ፡፡

አገሪቱን ባለፉት ሦስት ዓመታት ከገጠማት የፖለቲካ ቀውስና አለመረጋጋት ለማውጣት መንግሥት የተለያዩ ዕርምጃዎች እየወሰደ ቢሆንም፣ ችግሮቹ መልካቸውን እየቀያየሩ የቀጠሉ ይመስላል፡፡ የ‘ጥልቅ ተሃድሶ’ የፓርቲና የመንግሥት ግምገማ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ አስተዳደራዊ ዕርምጃዎችና የፀረ ሙስና ዘመቻዎች አገሪቱን ወደ ነበረችበት መረጋጋት መልሰዋታል ለማለት አዳጋች ነው፡፡

በቅርቡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት፣ የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነው፡፡ ኮንፈረንሱን ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

  • ለሁለቱም ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያላግባብ ክፍያ መፈጸሙ ተገልጿል
  • ሳትኮንና ሀዚ አይአይ ሥራ ተቋራጮች በክሱ ተካተዋል

ከሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው በከረሙት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሰባት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገምሹ በየነ (በሌሉበት) እና በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ማሞ (በሌሉበት) ላይ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

  • በገንዘብ ሚኒስቴርና በስኳር ኮርፖሬሽን ተጠርጣሪዎች ላይ የመጨረሻ ቀጠሮ ተሰጠ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት፣ ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዓቃቢያነ ሕግ ላይ የመጨረሻ የተግሳጽ ቅጣት ሰጠ፡፡

Pages